“አከባቢያችንን እንጠብቃለን ሰላማችንን እናመጣለን “በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ዕለት የእንጅባራ ከተማ ወጣቶች በወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከክልል፣ ከዞንና ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር መክረዋል።
“ወጣቶች አሁን የገጠሙንን ክልላዊ ፈተናዎች ማሻገር የሚችል እምቅ አቅም አላቸው” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
“አከባቢያችንን እንጠብቃለን ሰላማችንን እናመጣለን “በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ዕለት የእንጅባራ ከተማ ወጣቶች በወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከክልል፣ ከዞንና ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር መክረዋል።
የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ አቶ የኔአለም ዋሴ እንደገለፁት ወጣቶች ሀገርን በመገንባት ረገድ የጎላ አስተዋፅኦ አላቸው ። አያይዘውም ወጣቶች ዛሬም እንደትላንቱ ክንዳቸውን አስተባብረው የገጠመንን የፀጥታ መደፍረስ ለማስተካከል ከፀጥታ ሀይሉ ጎን እንዲሰለፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የአሚኮ አማካሪ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ፥በውይይት መድረኩ የእንጅባራ ከተማ ወጣቶች ተልዕኮ የሚወስዱበት ለሀገራዊ ፣ለክልላዊ እና ለከባባዊ ሁኔታ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጣና ክልሉ የተረጋጋ እንዲሆን አስተዋፅኦ ማድረግ አለበት ብለዋል። አያይዘውም መደበኛ ስራ ለመስራት የሚያስችል አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠርና ዘላቂእና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ወጣቶች ሚናቸውን መወጣት እንደሚገባቸውም አቶ ግዛቸው ጠቁመዋል ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የልማት ጉዟችን ወጣቱ ክፍል ብዙውን የህብረተሰብ ድርሻ ይይዛል ያሉት አቶ ግዛቸው ይህ ሀይል ከተባበረ የገጠመንን ችግር መሻገር የሚያስችል እምቅ አቅም እንዳለው ነው የገለፁት።ስለሆነም የነገ ሀገር ተረካቢ የእንጅባራ ከተማ ወጣቶችም አቅማቸውን በመጠቀም አሁን የገጠመንን ክልላዊ ፈተና ለመሻገር ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል ።
የውይይት የመነሻ ጽሁፍ ያቀረቡ የአዊ ብሄ/አስ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ፓለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዘለቀ ከፋለ በአዊ ብሄ/አስ የተፈጠረው የሰላም እጦት በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ፣በስነልቦናና መሰል መስተጋብሮች ላይ ጫና ፈጥሯል።አሁን ላይ ያለውን አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማሸጋገር ፣ የአካባቢን ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅና የከተማውን ልማት ለማፋጠን ወጣቶች የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው።
እርስ በእርስ በመገዳደል የሚፈታ ችግር የሚፈጠር ክልላዊ አንድነት የለም ያሉት አቶ ዘለቀ አባቶቻችን ያወረሱን እሴት ለኢትዮጲያዊነት እና ለሀገራዊ ግዛት አንድነት መሞት እንጂ ፅንፈኝነትን አይደለም ብለዋል።
ስለሆነም በከተማችን የተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲሰሩና እንጅባራ ከተማ ሰላሟ ተጠብቆ እንዲቀጥል የፀጥታ አካላት፣ ማህበረሰቡ በተለይም ወጣቶች በጋራ በቅንጅትና በርብርብ በመስራታቸው መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም ችግሮች ሊፈቱ የሚገባቸው በውይይት እንጅ በመጠፋፋት አለመሆኑን ጠቁመው ሰላማችንን ለማስቀጠል ክፍተቶችን ማረም፣ ሰርጎ ገቦችን መከታተል፣ የኬላ ፍተሻውን ማጠናከር ፣ ለሚመለከተው አካል የመረጃ ምንጭ መሆን እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር እንደሚገባም አቶ ዘለቀ ተናግረዋል ።
በዞኑና በእንጅባራ ከተማ ከሰላም ማስጠበቅ ጎን ለጎን የተሰሩ የልማት ስራዎችም አበረታች ሲሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል ።
የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በሰጡት አሰተያየት
በእንጅባራ ከተማም ብሎም በብሄረሰብ አስተዳደሩ አንፃራዊ ሰላም መምጣት የፀጥታ ሀይሉ እየሰራቸው ያሉ በጎ ተግባራት መጠናከር አለበት ። አሁን ከገጠመን ችግር ለመውጣት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር እና የመልካም አሰተዳደር ችግሮች ለመፍታት መንግስት ትኩረት ማድረግ ይጠበቅበታል። ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንም ሀላፊነታቸውን ሁሉ እንደሚወጡ ገልፀዋል።
