የአማራ ወጣቶች ማህበር የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ፤
የአማራ ወጣቶች ማህበር በክልሉ ውስጥ እና ውጭ የሚገኙ ወጣቶች ማህበራዊ ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ የሚሰራ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጂት ነው ያሉት የአማራ ወጣቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ወጣት ጋሻው አዘነ ውይይቱ ያስጀመሩ ሲሆን በነበረው ውይይት በክልሉ ያሉ ሁሉም ዞን ከፋተኛ የመፈፀም አቅማቸው እያደገ መሆኑን የታየበትና በቀጣይ ወራቶች ከዚህ በተሻለ ስራዎችን በመፈፀም የታቀደውን አመታዊ እቅድና የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ እውን ማድረግ እንደምንችል የታየበት የውይይት መድረክ ነው።በተጨማሪም ማህበሩ በሩብ አመቱ ከፋተኛ ውጤት ላስመዘገቡት
1ኛ.ሰሜን ጎጃም ዞን አማራ ወጣቶች ማህበር አንደኛ ደረጃ
2ኛ.ምስራቅ ጎጃም ዞን አማራ ወጣቶች ማህበር ሁለተኛ ደረጃ
3ኛ.ደቡብ ወሎ ዞን አማራ ወጣቶች ማህበር ሶስተኛ ደረጃ
እውቅና በመስጠት እና የቀጣይ ስራችን የአባላት ክፍያ፣አዲስ አባል ማፋራት፣ከፕሮጀክት እና ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች ሀብት በመሰብሰብ የማህበሩ የኢኮኖሚ አቅም ከፋ ማድረግ ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚያስፈልግ በመስማማት ተጠናቋል።
አዲስ እይታ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ትውልድ
አማራ ወጣቶች ማህበር
