ስለ ማህበሩ

የአማራ ወጣቶች ማህበር ለማናቸውም የፖለቲካም ሆነ የሀይማኖት ተቋማትና ድርጅቶች የማይወግን ፤ ነፃ ማህበር ሆኖ በሚመለከታቸዉ አካላት እዉቅናና ፈቃድ በአዋጅ ቁጥር 194 መሰረት ፤ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል በ1995 ዓ.ም የተመሠረተ ማህበር ነው።

ራዕይ

የክልሉ ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ችግሮች ተቀርፈው ብቁ ሀገር ተረካቢ ስራ ፈጣሪ አምራች ከውጤቱም ተጠቃሚዎች ሁኖው ማየት

ተልዕኮ

የክልሉ ወጣቶች በጠንካራ አደረጃጀት በማሳተፍ በስራ ፈጠራና ችግር አፈታት ሁለገብ የአቅም ግንባታና አድቮኬስን በመስራት ከሚመለከታቸው ተባባሪ አካላት ጋር ጽኑ ግኑኙነት በመፍጠር የሰለጠነ የረጃ አጠቃቀምና አደረጃጀት በመፍጠር የክልሉ ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ፖለቲካዊ ችግሮች ተቀርፈው ፍታሀዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡

ግብ

የወጣቶችን የልማት ሰራዊት በመገንባት ሒደት በተለይ የማህበራችን አባላት እና አመራሮች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ በሒደቱም የወጣቱን የግንዛቤ ደረጃ በማሳደግ፤ መዋቅራችን የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ በሚያስችለው ቁመና ላይ እንዲገኝ አልሞ በመስራት ጠንካራ የልማት ሰራዊት መገንባት፡፡ የሚገኙ የማህሩ አባላትን የንቅናቄ መድረክ በማዘጋጀት ሰፊ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና በመስጠት ነፃ፣ ፍትሐዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ገለልተኛ፣የመራጮችን ታማኒነት ያረጋገጠና ከድምጽ ማጭበርበር ነፃ የሆነ ምርጫ እንዲሆን ማድረግ።

Scroll to Top