“የተደራጁ ወጣቶች የሰላም፣የዲሞክራሲና የልማት አቅም ናቸው” አወማ !!

የማህበሩ አመሰራረት

 

የአማራ ወጣቶች ማህበር ለማናቸውም የፖለቲካም ሆነ የሀይማኖት ተቋማትና ድርጅቶች የማይወግን ፤ ነፃ ማህበር ሆኖ በሚመለከታቸዉ አካላት እዉቅናና ፈቃድ በአዋጅ ቁጥር 194 መሰረት ፤ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል በ1995 ዓ.ም የተመሠረተ ማህበር ነው።

ወጣት ጋሻው አዘነ ሙሉ

የአማራ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት

የዞን ቅርንጫፎች

አዳዲስ ዜናዎች

Gamble Starburst no deposit bonus wheel of fortune Slot 100
BlogsStarburst On the Portable- Android os, new iphone, And you...
Maple Leaf Forever step one ounce Absolute Precious metal Money
Content Sort of No-deposit Bonuses Told me | savannah king...
Spielsaal Prämie bloß Einzahlung August 2026
Ja lärmig deutschem GlüStv darfst respons je Spielrunde schlimmstenfalls 1...
Tranquility ice casino login Canada
Posts Ice casino login Canada – Serenity Servers Faq’s The...

የማህበሩ ፕሮግራም

ስለ ህገ-ወጥ ስደት ግንዛቤ መስጠት

ህገወጥ የሰወች ዝውውር የሚያስከትለውን ጉዳት በተመለከተ ለ10,000 ሽህ ያህል ወጣቶች ግንዛቤ መፍጠር፣ወጣቱ በሃገሩ ሰርቶ መለወጥ እንደሚችል ትምህርት መስጠት።

በግብርና እና በከትሞች በሚካሄዱ ልማታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ሁሉንም የማህበሩ አባላት በተደራጀ መንገድ ተሳታፊ ማድረግ፤በተፈጥሮ ሀብት ስራ የዳኑ እና ያገገሙ ተራሮችን መጠበቅና መንከባከብ ላይ የማህበሩ አባላት የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል።በገጠር የእርሻ መሬት ለሌላቸዉ ወጣቶች ከሚመለከትዉ አካል ጋር በመነጋገር መሬት የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸትና 20,000 የማህበሩን አባላት በመስኖ ስራ እንዲሰማሩ ማድረግ። ከቴክኒክና ሙያ ኢንተርኘራይዞች ልማት ጋርና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመነጋገር 15,000 ለሚሆኑ የከተማ የማህበሩ አባላት የስራ እድል መፍጠር፣ በማህበር ተደራጅተው ስራ በመሰራት ላይ የሚገኙ አባላትን መደገፍ፣ የብድር የመሰሪያ ቦታ ጥያቄወች ያለምንም ቢሮክራሲ ምላሽ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት።

በየደረጃው ባሉ መዋቅራችን የፀረ-ሙስናና ስነ-ምግባር ክበባትን ማቋቋም! በብልሹ አሰራር እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ለማህበሩ አባላት እና ለዞንና ለወረዳ አመራሮች የክልል አጋር አካላትን በማስተባበር ስለፀረ ሙስናና ብልሹ አሰራር ትግል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት።ከዚህ በተጨማሪም ከየትኛውም ፖለቲካ ፖርቲ ነፃ የሆነ አደረጃጀት በመፍጠር በቀጣይ 2018 ዓ.ም የሚካሄደዉን 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በክልላችን በሁሉም አካባቢዎችና በአዲስ አበባ

ስለ አደገኛ መድሀኒቶች እና እፆች ጐጅነት እንዲሁም ይህን ተከትለው ስለሚመጡ እንደ ኤች አይ ቪ እና መሰል የጤና ቺግሮች ለአባላት እና 500,000 ለሚሆኑ ወጣቶች ግንዛቤ መፍጠር፤ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመተባበር ወጣቶች ነጻ የትምህርት እድል እንዲአገኙ ማስቻል፤የወጣት ማዐከላት እንዲገነቡ፡ከዚህ በፊት የተገነቡትንም ማጠናከር እና ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል።

አጋሮቻችን

ያግኙን

Scroll to Top