ባህርዳር ፡ የካቲት 23/2018 ዓ.ም (አወማ) የአማራ ወጣቶች ማህበር ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ማስጀመሪያ ፕሮግራም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።
በቴክኖሎጅ ራስን በመቻል ውጤታማ ተግባቦትን መፍጠር ያስፈልጋል።
ባህርዳር፡የካቲት23/2018ዓ.ም(አወማ)የአማራ ወጣቶች ማህበር ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ማስጀመሪያ ፕሮግራም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።
በም/ርዕሰ መስተዳድረ ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክብር እንግዶች ተገኝተው የማህበሩን ሚዲያና ኮሙኒኬሽን በይፋ አስጀምረዋል።
የአማራ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝደንት አቶ ጋሸው አዘነ በዲጅታል ስርዓት እራሳችን በመቻል የማህበሩን ግብና አላማ ማሳወቅ እና ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የድጅታል ሚዲያና ኮሙኒኬሽን አቋቁመናል ብለዋል።
የማህበሩ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን መጀመሩ ለወጣቶች ጠንካራና ውጤታማ ተግባቦትን መፍጠር ያስችለናል ሲል አቶ ጋሸው አዘነ ተናግረዋል።
የማህበሩ ዋና ፀሐፊ አቶ ሙላት ባይሌ የማህበሩ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን የራሱ የሆነ ተልዕኮ ያለው እና ጠንካራ የሚዲያ ግንኙነት በመፍጠር ለወጣቶች ሁለንተናዊ ለውጥ የሚተጋ ተወዳዳሪ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን እንዲሆን ማድረግ አለብን ብለዋል።
በመርሐግብሩ የማህበሩ አዲስ ድረ ገጽ የተዋወቀበትና አባላት መመዝገብ ሲያስፈልጋቸው ወደ ቀበሌ መሄድ እንደማይጠበቅባቸው ያስገነዘቡት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ሀብቴ በተጨማሪም በድረ ገጱ ማህበሩ ምን እየሰራ እንደሆነ ቀን በቀን መከታተል ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።
