የአማራ ክልል ሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የክትትልና ደጋፍ ቡድን ከባህር ዳር ወጣቶች ጋር ውይይት አደረገ።

የአማራ ክልል ሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የክትትልና ደጋፍ ቡድን ከባህር ዳር ወጣቶች ጋር ውይይት አደረገ።

ባህርዳር 30/6/2018 (አወማ)የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር “ለሰላም ዘብ እንቆማለን፣ የልማት አርበኛ እንኾናለን” በሚል መሪ ሃሳብ ከልዩ ልዩ የአደረጃጀት መሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ሰብለ ዘውዱ ወጣቶች ለሰላም የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል።

ወጣቶች አባቶቻቸው ያስረከቧቸውን ሀገር ሉዓላዊነቷን በመጠበቅ፣ ኢኮኖሚውን በማሳደግ፣ በልማት እና በሰላም እንቅስቃሴ ላይ ንቁ ተሳታፊ በመኾን ሀገርን ማሳደግ እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።

የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚተጉ ያነሱት ወጣቶቹ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ እንደሚሠሩም አስረድተዋል።

የቀጣይ የሀገር ሉዓላዊነት በወጣቶች እጅ ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ ሰላማዊ ምርጫ እንዲከናወን እንተጋለን ብለዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top